ለግጥምጥም…!

ደርዘን በሞላ ቀን፣
ደርዘን በሞላ ወር፣ 1
በኮራ፣ በደራ፣ በ12..12..12.. ድርደራ፣

በፈረንጆች ስሌት. . . በፈረንጅ ቆጠራ፣
ሁለት ሺ ደፍኖ፣ ደርዘን ባ’ከለ አመት፣
የደርዘን ዙር ፍቅሬን… እነሆኝ ልዘክር፣
ላ’ባዛ፣ ላ’ካፍል፣ ልቀንስ፣ ልደምር፣
የፍቅርሽን ብዛት፣ የውድሽን ስፍር…
ቤት ውዬ ልቀምር…፤
ተረጂኝ ዓለሜ – እርጂኝ የ’ኔ ፍቅር… Silhouetted Woman Running at Sunset
ገስግሽ ወደ ቤቴ፣ ጓዝሽን ሸክፈሽ፣
ለቆጠራ ብቁ – አለ – ያልሽውን ይዘሽ፣
ትዝታሽን አዝለሽ፣ ተስፋሽን ሰንቀሽ፣
ድረሽ ከመደቤ፣ ተጠጊ ከልቤ፣
ዝለቂ ሰፈሬ፣ ግቢ ከመንደሬ፣
በእንዲ’ ያል የቀን ማማር፣
….በእንዲ’ ያለ ግጥምጥም፣
ካንቺ ይሁን ውሎዬ፣
….ካንቺ ይሁን አዳሬ፤እንዲያው ለግጥም ጥም
…ቃላት ሳበላልጥ፣ ቃላት ሳለካካ፣
ቃል ከቃል ሳጋጥም፣ አንጀት እንዲያረካ፣
እንዲሆን ለውሀ ጥም
– ምናልባት ከጠማን፣ ከቤት እንዳንወጣ፣
– ውሀ ምናባቱ!… ግጥም እንድንጠጣ፣
እንዲጥም፣ እንዲጥም…ልግጠምልሽ ደሞ…
እንዳልታየ ሰምሮ፣ እንዳልታየ ገጥሞ፣
ቃል ከቃል ተሳስሮ፣ እንደማያውቅ ቀድሞ፣
ቶሎ ነይ ዓለሜ!

እነሆ ቀለሙ፣… እነኋት ሀረጓ…
እነኋቸው ቃላት፣… እነሁልሽ አንጓ…
እነሁልሽ ብዕር… ሊገጥም ሲያዛጋ፣
ደግሞም…untitled
ወር ገብቶ በሰለስት፣ በሶስተኛ ቀኑ፣
በወር በአራተኛው…
ሁለት ሺህ አምስት… በሞላ ዘመኑ፣
– ‘ዘመነ ምህረት’…በሀበሾች ቆጠራ፣
ምህረት ይሁንልን፡፡

በሀበሾቹ ብቻ…
ሶስት እንትን ትዝታ፣
አራት እንትን ፍቅር፣
አምስት እንትን ተስፋ፣
ስድስት እንትን አንቺን… ደግም ከዚያ በላይ፣
የፍቅር አዱኛን፣… የመውደድን ሲሳይ፣
ሸክፈሽ ድረሺ…፤

በድርድር ሲቀመጥ፣ ቁጥር ተነባብሮ፣
ቀን ወር ተሰማምሮ፣ በዓመት ተጠፍሮ፣
እዪማ ዓለሜ…
…ሲያምር፡ – ለዐይን ለጆሮ…
3… 4… 5… እርሱ ራሱ ግጥም! — ሲጥም!
6ኛም አንቺ፣ – ‘የገጣሚው ንግስት፣
አጋጣሚ ዛሩ፣…ሂጂለት ከቤቱ፣
እየጠበቀሽ ነው፣ አጋጥሚው በሞቱ…’
…ይበሉሽ ሰዎቹ!
ተነሽ እመቤቴ፣
ብቅ በይ ከቤቴ፣
ምጪልኝ በሞቴ፡፡

ስራ የፈቱ ነጮች፣ ሚገጥሙለት ያጡ፣ እንደተነበዩት…
ምናልባት ከመጣ፣ በፈረንጆች ማርያም፣ በ21/12/2012፣
አንቺ ወዲያ ማዶ፣ እኔ ወዲህ ማዶ…
እንዳላስቀመጠን፣ አጉል ተበታትነን፣
እንዳያጣን ድንገት:-
— ከቤት ከቦታዬ፣ ከቦታሽ ከጎኔ…
ሲፈልግ አግኝቶን
— ካላሰበን ቦታ፣ እንዳይሆን ኩነኔ፣
በይ ነይ ላንቆላጵስሽ…

ቃል እየመራረጥኩ፣ ሌሊቱ እስኪነጋ፣ romance
የግጥምጥሞሹን፣ – ልግጠምልሽ በቃ፣
እስኪደርስ ቀኑ፣ አምላክ እስኪመጣ፣
እንበል ‘ማራናታ’፣
ባልነው ስራ የለም…
…እነሁልሽ ሰንበት፣ እነኋት በዓታ፣
– የታህሳስ በዓታ፣ ነጋሿ – የአመቷ…

ለውድሽ በረከት፣ ለፍቅርሽ ስጦታ፣
ስንኙን ላሰናኝ፣ ቤት ከቤት ላማታ፣
ወርቁን ሰም ልቀባ፣ ቅኔ ልሰር ልፍታ፣
አበርቺኝ ልበርታ፣ ይሁንልን ፌሽታ!
ዓለሙን ይግረመው፣ አንቺንም ይግረምሽ፤
እኔንም ይግረመኝ…፤
በይ ነይ ልግጠምልሽ! ልበልሸ ባይገርምሽ፤
ባይገርምሽ….ባይገርምሽ….ባይገርምሽ….

/ዮሐንስ ሞላ/
12/12/12
03/04/05 Only  Ethiopian

2 thoughts on “ለግጥምጥም…!”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s