አይደብርም?!

ከዚህ በፊት በተለያየ ጊዜ ብዙ የሀሰት ምስክርነቶችን ሰምተናል፡፡ እንደ ምሳሌ፡ ‘የተኩላው ለምድ ሲገፈፍ‘ የሚል ቪዲኦ ላይ መንገደኛ የኔ ቢጤን ‘አቡን ነበርኩ’ (አቡነ ያሬድ) አስብለው… ኋላ ላይ ‘ጌታን ተቀበለ’ ተብሎ ትልቅ ፌሽታ ሲደረግ የሚያሳይ ምስል ታይቶ….ቆይቶ ነገሩ ሲጣራ ግን ሰውየው የኔ ቢጤ እንደነበር እና ተክፍሎት እንደሆነ ታወቀ፡፡ በርሱም ብዙ አልን፣… አስባልን፣… ተባባልን….

እነሆ አሁን ደግሞ ኤርሚያስ የተባለ ሰው በቴዲ ድምፅ አስመስሎና የቴዲ እንደሆነ አድርጎ መዝሙር ለቅቆ…. ‘ቴዲ አፍሮ ፕሮቴስታንት ሆነ’ ተብሎ በሰፊው እየተወራ ነው፡፡ — ውስን ፕሮቴስታንቶችን እያስፈነጠዘ….ውስን ኦርቶዶክሶችን እያሳዘነ…. አሉባልተኞችን ደግሞ ወሬውን እያስቀባበለ…

ዘማሪው ያን ማስባል አለማስባሉን (እንዲባልለት መፈለግ አለመፈለጉን) …ወይም በርሱ እውቅና መደረጉን አላውቅም፡፡ ሆኖም ግን ቴዲን ለመምሰል በእጅጉ ደክሟልና፣ መመሳሰሉ ሆን ተብሎ አይደለም ለማለት ይከብዳል፡፡ እንዲያው ለጨዋታ ያደረገው ጎረምሳ ነው እንዳንል ደግሞ፣ ጥንቅቅ ተደርጎ በመሳሪያ የተቀናበረ ቆንጆ ድምፅ ነው የሚሰማው፡፡

ግን በውሸት ይህ በመሆኑ አትራፊው ማነው? የምሩን ጠፍቶ ሲሆን በአንድ በግ መገኘት (መመለስ) በሰማይ ትልቅ ደስታ እንደሚደረግ እናውቃለን (እናምናለን) …ግን በእነዚህ የሀይማኖት ሰዎች (ሀላፊዎች) ዘንድ በአንድ ሰው እምነቱን መቀላቀል ወሬ ስንት ብር ይሆን የሚገኘው? የቴዲ ፕሮቴስታንት መሆን ፕሮቴስታንቱን ያጠነክረዋልን? ኦርቶዶክሱንስ የላላዋልን? …ያም ይቅር፣ የእግዚአብሔርን መታመን ይወስነዋልን? በዚህስ ምን ያህል ሰው ለማትረፍ ታስቦ ይሆን?…

በእውነት እንዲህ ያለው ዘመቻ የሚደረገው በሀይማኖት አባቶችና አገልጋዮች እውቅና ከሆነ  በጣም ያሳዝናል፡፡ — በዛሬ ማዳን ሰበብ ከነበሩበት ጎዳና አስወጥተው መንገድ ላይ በአውላላው ስለሚጥሏቸው ነፍሳት አላሰቡምና፡፡ በዚያም ላይ በራሱ አፍቃሪ – ቴዲዎችም አሉና… ያም ሆነ ይህ ድርጊቱ ነውር በመሆኑ ሊወገዝ ይገባዋል፡፡

እጓለ ገብረ ዮሐንስ የተባሉ ሊቅ በ1956 ካሳተሙት “የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ” ከተሰኘ መፅሀፍ ላይ ይህቺን ጠቀሼ ላብቃ፡፡…

“ባሮጌ ቤት የሚኖረውን ሰው ተጥግቶ ቤትህ የማይረባ ነው ማለት አይገባም፡፡ ከበረቱ አጠገብ አዲስ ቤት መስራት ነው፡፡ ይህ አዲሱ ቤት ስለራሱም አዲስነት ሰለሌላውም አሮጌነት ይናገራል፡፡….እውነት የራስዎም የውሸትም ማስረጃ ናት”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s