ከየትኛውም ወገን፣ በየትኛውም ቦታ ለመወለድ ማንም የራሱን አስተዋፅኦ አላደረገም፤ ምንም ነገርም አላዋጣም። እንኳን ብሔሩን (ዘሩን) ማንም ወላጆቹንም መርጦ አልተወለደም። ሌላው ቀርቶ ለ’ሰውነት’ም የታሰበው እርሱ መርጦና ፈቅዶ አይደለም።…እርስ በርስ በመበላለጥና በመናናቅ ስሜት ውስጥም ባዶ ትምክህት እንጂ ማንም ሌላ ምንም መሰረት የለውም። ስለሆነም…
እርስ በርስ በዘር መጦዛጦዝ፣ እንዲሁም ንግግርን ሁሉ በዘር በመመንዘርና በመዘርዘር እርስ በርስ መናቆርና ማናቆር እጅግ በጣም ኋላ ቀርነት ነው። እናም ይቅር። አእምሮአችንን እናፅዳ። ሌላው ሌላው ነገር ከቁጥጥራችን ውጭ ሆኖ መወራረሱ ቢከብደን፥ ቢያንስ ከዘረኝነት የፀዳች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እናቆይላቸው ዘንድ ቅንነት ካለን በቂ ነው።
“በአያቴ በር በኩል ማን እንዳለፈ አላውቅምና ዘሬን አትጠይቁኝ” (ሀሳቡን ነው እንጂ ቃል በቃል አላስታወስኩትም) ~ ሰለሞን ደሬሳ
Photo source: internet