እሷም እሷም የእኛ!

ብርቅዬዎቹ አትሌቶች፥ ጥሩነሽ ድባባና መሰረት ደፋር አብረው በሮጡበት ጊዜ ሁሉ የሚታወስ አንድmeseret-defar-tirunesh-dibaba-2009-9-12-15-41-34 ቅፅበት አለ… — የሴፕቴምበር 3/2006 የበርሊን ጎልደን ሊግ ውድድር መጨረሻው። ብዙዎች (ተሳዳቢዎች) መሰረትና ጥሩነሽን ለማበላለጥ፣ እንዲሁም መሰረትን በማይረቡና ጥላቻን በሚያንፀባርቁ ቃላት ለማብጠልጠል የሚያስታውሱት ጊዜም ያንን የበርሊን ውድድር የመጨረሻ ቀን መሰረት ጥሩነሽን መቅደሟንና ጥሩነሽ ከጃክፖቱ ሳትቋደስ መቅረቷን ነው።

በርግጥ በእድልና በአጓጉል አቋራጮች መብለጥና መሸለም፣ በዘመድና በእጅ መንሻ የማርያም መንገዶችን ማበጀት በለመደ በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ የመሰረት ዓይነት ድርጊት ከተንኮል ነው የሚቆጠረው… ማሸነፍ ከመጥፎ ድርጊት ተቆጥሮ፣ ስግብግብ ነው የሚያሰኘው… በሀቅና ራስን ችሎ መሮጥ ከነውር ነው የሚመደበው።

እስከ መጨረሻው ራስን ችሎ መስራትና እርስ በርስ መፎካከር፥ እንዲሁም ራስን ማክበር ከግምት አይገቡም… ጥሩነሽ ቦታ ያለም ሰው ነገሩን እርሷ እንተረዳችው በቅንነት አይረዳውም። …ለነገሩ ከእነርሱ ቦታዎች ውጭ ሆነን እነርሱ አንዴ ያደረጉትንና ረስተውት እርስ በርስ የሚዋደዱትን፥ እኛ ከ7 ዓመታትም በኋላ አስታውሰን፥ ጥላቻ እየዘራንበት አይደል?!

ፉክክራቸውን ከዓለም ጋር ፈፅመው ሲያበቁ እርስ በርስ በመፎካከራቸውና መሰረት ቀድማ በማለፏ በወቅቱ ዓለም የተደነቀበት ጉዳይ ነው። ዛሬም ድረስ የምናስታውሰው ትዝታ ሆኖልናል… ክብረትና ሽልማቱ እንደው ለእነርሱ፤ ትዝታው ይትረፈን እንጂ… እሷም እሷም የእኛ! በወቅቱ ጥሩነሽ የቀደሙትን ሩጫዎች ሁሉ ጨርሳ፥ የመጨረሻው ሲቀራት፥ ሲቀራት መሰረትን የእሁዱን ሩጫም ዝግ እንድታደርገው ውለታ እንደምትጠይቃት በጨዋታ ሲያግባቧት….

“ይህንን በጭራሽ አላደርገውም። ባደርገው እንኳን፥ እርግጠኛ ነኝ መሰረት በእንደዚህ ዓይነት ድርድር አትስማማም። …እኔም እርሷም ለማሸነፍ ነው የምንሄደው። ምንም ዓይነት አቋራጭ አይኖርም። እኔና መሰረት አብረን ስንሮጥ፥  ለ11 ከ½  ዙሮች ድረስ እርስበርስ ተያይተንና ተጠባብቀን ነው። የሚለየን የመጨረሻው ዙር ነው። በመጨረሻው ዙር ላይ የሚኖረው ምርጡ ሯጭ ደግሞ፥ አሸናፊ ይሆናል።”

ብላ ነበር። (AIPS media)

ሌላ ሌላውን ትተን፥ በዚህ በጥሩነሽ ንግግር ካየነው፥ ምንም ዓይነት እርዳታና አቋራጭ እንደማትፈልግ የገለፀችውን ልጅ፥ መሰረትን ‘ለምን oly_london_19አቋራጭ አላበጀችላትም፣ ሩጫውን አልተወችላትም?’ ብሎ መውቀሱ ኋላ ቀርነትና ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ መሆን ነው። ከዚህ በተጨማሪም፥  ራሷ ጥሩነሽ አያይዛ ስትናገር

“ገንዘብ ከክብርና ከዝና ቀጥሎ የሚመጣ ሁለተኛ ነገር ነው።”

ብላ ነበር፥ ታዲያ ራሷ ጥሩነሽ ደረጃ መድባለት ከገንዘብ ክብርና ዝና ይቀድማሉ ባለችበት ጉዳይ ላይ…. መሰረትን ‘ስለጥሩነሽ ገንዘብ ብላ ዝናና ክብሯን ለምን አልተወችም?’ ብሎ መውቀሱ አለማወቅ ነው።

ጥሩነሽ ስትቀጥልም፥

“የምሮጠው ለስሜና ለገፅታዬ ነው። አሰልጣኛችን ቶሎሳ ቆቱ በቴሌቪዥን ቀርቦ እስኪያብራራ ድረስ ስለጃክፖቱ አከፋፈል የማውቀው ነገር አልነበረም። …እናም ለገንዘብ ስል በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ አላልፍም። እኔ የምሮጠው ለዝና ስል ነው።”

ብላ መልሳ ነበር። ታዲያ ይህ በሆነበት ቦታ ላይ ጥሩነሽ ያለመችለትን ዝና መሰረትም በችሎታዋ  ማግኘቷ ምን ነበር ችግሩ?

ቀጥላ፥ ጥሩነሽ ስለ ጃክፖቱ የመጀመሪያ የፓሪስ ውድድርና ስለመሰረት ስትናገርም፥

“በሩጫ ዓለም እስከዛሬ ከገጠሙኝ ውድድሮች ውስጥ በጣም ከባዱ ሩጫ ነበር። በዚህ ወቅት ሁለታችንም ጥሩ ሁኔታ ላይ ነበርን።… ብዙ ሰዎች እንደሚያስቡት እኛ ጠላት አይደለንም። ከሩጫው መም ውጭ በጣም ጥሩ ጓደኛሞች ነን። እንደ እህቴ ማለት ናት።”

ብላ ነበር። ታዲያ ስለምን እነርሱ መካከል ገብተን እንብሰከሰካለን? ያልተገቡ ቃላትንስ ስለምን እንናገራለን?

ማስታወሻ: ይህንን የምለጥፈው በinboxም በውጭም አስቀያሚ ንግግሮችን የሚናገሩና መሰረትና ጥሩነሽን በዚህ ደረጃ ወርደው ጥላቻ የሚዘሩ ሰዎችን ተመልክቼ ነው። በበኩሌ ከሁለቱም ጋር ፀብና ዝምድና የለኝም። ሁለቱም የሀገሬ ሰዎች እንደመሆናቸው ሁለቱም ሲያሸንፉ ሀሴት አደርጋለሁ።

መሰረት ስታሸንፍ፥ ጥሩነሽን አላንቋሽሽም፣ ችሎታዋን እያነሳሁ እየጣልኩ የመሰረት ማሸነፍ አግባብ እንዳልሆነ አልናገርም። ጥሩነሽ ስታሸንፍም መሰረትን አላንቋሽሽም፣ ችሎታዋን እያነሳሁ እየጣልኩ የመሰረት ማሸነፍ አግባብ እንዳልሆነ አልናገርም። ሁለቱም የምኮራባቸውና፥ ‘እንኳን ኢትዮጵያውያን ሆኑ’ የምልላቸውና ከልቤ የምወዳቸው አቦሸማኔዎቼ ናቸው።

One thought on “እሷም እሷም የእኛ!”

  1. Yeliben yezewetr hasab neaw yegeletskew. Ke wendmoche gar enkuan yaltesmamahubet guday neber. Eyetah des blognal. Thank You!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s