የፌስቡክ ግሩፕ ውስጥ፥ ሰዎች ፈልገው ብቻ ሳይሆን ግሩፑ ውስጥ ባሉ አባላቶች add ስለሚደረጉ (ወደ ግሩፑ ስለሚገቡ) …አባል የሆኑት፥ በትክክል አምነውትና ጉዳዩን ለይተውት ይሁን፥ ዝም ብለው ወደ ግሩፑ ስለገቡ፥… ምንም አይታወቅም።
ቀላል የሂሳብ ምሳሌ፥… Jawar Mohammed 5000 ጓደኞቹን፣ Daniel Berhane እንዲሁ 5000 ጓደኞቹን፣ Alula Solomon እና Abiy Atomssaም ጓደኞቻቸውን፥ ሌሎች አራጋቢዎችና ጠብ አጫሪዎችም እንዲሁ ያሏቸውን ጓደኞች ሰብስበው ቢያዋጡ፥ ግሩፑ በተከፈተ 1 ሳምንት አይደለም፥ …የinternet ኮኔክሽን ችግር ካልገጠመ በቀር፥ በተከፈተ በአንድ ቀኑም 37, 000 አባላት ሊኖሩት ይችላሉ።
ስለሆነም፥ የፌስቡክ ግሩፕ አባላት ብዛት፥ ስለ ግሩፑ ጥንካሬና ወደው ስለሚከተሉት አባላቶቹ የሚነግረን አንዳችም ነገር የለውም። ይሄ “…በምርጫም ሆነ በአማራጭ ማጣት፥ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ90 ሚሊየን በላይ ብዛት ያለው ሕዝብ፥ ኢህአዴግ በሚያስተዳድረው ግዛት ውስጥ ስለሚኖር፣ የመንግስት ማኅበራዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ስለሆነና፥ ሀገር ውስጥ ሰርቶ ለመንግስት ግብር ስለሚከፍል፥ የመንግስት ወዳጅና ደጋፊ ነው።…” ብሎ ከመደምደምና ሰዎችን ከማደናገር ያልተናነሰ ውስልትና ነው። ….እንዲህ ባለ ሂሳብ ሰውን ለማታለልና ጆሮ ፍለጋ ማባበልም «እቆረቆርልሀለሁ፤ ተከተለኝ…» የሚሉትን ማኅበረሰብ መናቅና የማሰላሰል አቅሙን መገመት ነው የሚሆነው።
ይህንንም ይዞ፥ የግሩፑን እንቅስቃሴ ጎራ ብሎ የሚመለከት ሰው፥… ግሩፑ ውስጥ ያሉትን እንቅስቃሴዎችና ንቁ የጥላቻ ተሳትፎ የሚያደርጉ ሰዎች 50 ገደማ ብቻ እንደሆኑ መታዘብ ይቻላል። ለዚያውም በወረዱ ቃላቶች የተቀመሙ ስድቦችንና፣ በሕግም በኅሊናም ፊት በወንጀለኝነት ሊያስጠይቁ የሚችሉ የምስል ቅንብሮችን፥ ተቋቁሞ መቆየት ለቻለ ነው። (በነገራችን ላይ፥ አንድ ግሩፕ ውስጥ ያሉ ሰዎች ቃላቸውን መመጠንና ራሳቸውን መግራት አለመቻላቸው በራሱ የሚነግረን ትልቅ ነገር አለው።)
እኔ ከግሩፑ ውስጥ በጣም ትልቅ እንቅስቃሴ ተደርጎበት ያየሁት ልጥፍ (post): 249 like፣… 43 comment… እና 0 share ያለው ነው። ምናልባትም ብዙ ሰው ይሳተፋል የሚለውን ስሜት ለመፍጠር ሊሆን ይችላል፥ ይኸው ትልቁ ታይታ የገጠመው ልጥፍ (post) pin ተደርጎ የገባ ሁሉ ከአናት ላይ እንዲያየው ተደርጓል። …በአንፃሩ፥ Teddy Afro መጨረሻ ላይ፥ የሙዚቃ ጉዞውን በተመለከተ የለጠፈው post ላይ ያለውን የወዳጆቹን እንቅስቃሴ ስናየው፥ 895 like, 366 comment እና 110 share አለው።
እንዲህ ያለ የወረደ የሂሳብና የቆጠራ ስሌት ውስጥ የገባሁት፥ ጥላቻን ለመስበክ ወገባቸውን ቋጥረው ላይ ታች የሚሉ፣ ማኅበራዊ ድህረ ገፆች ላይ ሽብር የሚነዙና ሰዎች ድህረ ገፆቹ ላይ በሰከነ መንፈስ እንዲወያዩና እርስበርስ እንዲቀራረፁ የሚያውኩ ወዳጆች ሆይ ሆይታ በከንቱ እንደሆነ ብንገነዘብ ብዬ ነው። ጃዋር ካቅሙ (ከደረሰበት የቀለም ትምህርት ደረጃም አንፃር፥ ግሩፕ ውስጥ ያሉ አባላትን በመቁጠር ደረጃ መውረዱ ገርሞኝ ነው።) በትዊተርና በፌስቡክ ገጾቹ ላይ ቁጭ ብሎ…. የ #boycottbedele ግሩፕ አባላት ብዛት ይኽን ያህል ሆኑ፥ ይኽን ያህል ደረሱ እያለ ማቅራራቱን ታዝቤ ነው።
ትናንትና Soli S Gmichaelም እንዳለችው ግሩፕ በመሆን ፈንታ #fan_page ቢሆን ኖሮ ግን፥ ሰዎች (ሁሉም ባይሆኑም) መርጠው ስለሚገቡ፥ ዓላማውን ይደግፋሉ/አይደግፉም ብሎ ለመቀወጥ፥ ከግሩፕ የተሻለ አሳማኝ ሊሆን ይችል ነበር። ….ለዚህም እንደ ቀላል ማረጋገጫ፥ እነ አብይ አቶምሳ የከፈቱትን (እንደዛ ያልኩት አብይ ወደዛ ገጽ ከ1ም ሁለት ጊዜ invite አድርጎኝ ስለነበር ነው።) ገጽ የወደዱት (like ያደረጉ) አባላት 2509 ብቻ መሆናቸው ነው። ስለሆነም ሁሉም በማስተዋልና በመገንዘብ ቢሆን ወደፊት እርስበርስ ከመተፋፈር ይጠብቀናል።
የኤትኖግራፈር ተመራማሪውና ፀሐፊው Afendi Muteki ደግሞ በጉዳዩ ላይ እንዲህ ይላል “ወገኖቼ! አንዴ እንረጋጋ፡፡ እኔ የምላችሁን ስሙኝ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰከን ብላችሁ አስቡ፡፡ ሰዎች ገንዘብና ዝናን እያሰቡ መጠቀሚያ እያደረጓችሁ ነው፡፡ ከአሁን በኋላ የዚህን ወንጀል ቀንደኛ መሪዎች እናጋልጣለን፡፡ በህዝብ ደም ለመነገድ የሚያደርጉትን ብልጣብልጥነት በትዕግስት አናልፈውም፡፡ አንዳንዶቹ ከላይ ለኦሮሞ የሚቆረቆሩ እያስመሰሉ በድብቅ ግን እራሳቸው “ነፍጠኛ” እያሉ ከሚሰድቧቸው ቡድኖችም ጋር በሚስጢር እንደሚሰሩ ተጨባጭ ማስረጃ አለን፡፡ ወላሂ!! አስቡበት! ረጋ በሉ! በጨዋነት እንነጋገር!” (ሙሉውን ከእርሱ ገፅ አንብቡት።)
ሌሎችም እንዲሁ ነገሩንና ድብቅ አጀንዳውን በግልፅ እንዲረዱት፥ ካመንንበት፥ ሀሳቡን በማጋራት (share በማድረግ) እርስ በርስ እንጠባበቅ።
Ur Analysis Lack authentication since u beginn by linking The movemnt with eprdf. Who do u think will lose the most from this movemnt any negative News about investemnt will heart the gov the Most and would in million years gwt itself in to this.
If u real want to say sth about ist streangth See ans analyze the ground work.