አዝናለሁ | ሰምጫለሁ…

አዝናለሁ እናቴ… 27C7DFF500000578-3047013-image-a-1_1429530273746
መርከቡ ስለሰመጠ፣ ካሰብኩበት ደርሼ ከጉዞዬ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን እዳዎች መክፈል አልችልምና!

ሙት አካሌን ስለማያገኙት አትዘኚ። ለትራንስፖርት እና ለቀብር ወጪ ካልሆነ ላንቺ ምን ይረባሻል?

አዝናለሁ እማ…
ምንም እንኳን ህልሜ እንደ ሌሎቹ ትልቅ ባይሆንም፣ ጦርነት ወደ እኛ ስለመጣ እንደ እነርሱ ሁሉ መሸሽ ነበረብኝ። …እንደምታውቄው፥ ህልሜ ሁሉ ለትልቁ አንጀትሽና የጥርሶችሽን ጤና ለመመለስ በሚበቃ፣ በአንዲት የመድኃኒት ሳጥን ልክ የተወሰነ ነበር። በነገርሽ ላይ፥ እላያቸው ላይ ከተጣበቁባቸው ቅጠሎች (moss) የተነሳ፣ ጥርሶቼ አረንጓዴ ሆነዋል። ሆኖም፥ አሁንም ከአምባገነኖቹ አሳዳጆቼ ጥርሶች የተሻለ ያምራሉ።

አዝናለሁ ውዴ…
ፊልሞች ላይ እንዳየናቸው ከእንጨት የተሰራ፤ ከቦምብ ቀጠናዎቹ፣ ከጎጠኝነትና ከብሔር መድሎዎች፣ እንዲሁም ከጎረቤቶቻችን አሉባልታዎች የራቀ… የሚያምር፣ የማይጨበጥ የቅዠት ቤት ስለገነባሁልሽ!

አዝናለሁ ወንድማለም…
ከምረቃ በዓልህ ቀደም ብሎ ጥሩ የሆነ ጊዜ እንድታሳልፍ እንዲረዳህ፣ በየወሩ መጀመሪያ እንደምልክልህ ቃል የገባሁልህን 50 ዩሮዎች ልልክልህ ባለመቻሌ!

አዝናለሁ እህቴ…
ባልንጀራሽ እንዳላት ዓይነት፣ ዋይፋይ ያለው አዲስ ስልክ ገዝቼ ስለማልክልሽ!

አዝናለሁ የኔ ውብ ቤት…
ከእንግዲህ ከበርህ ጀርባ፥ ኮቴን አልሰቅልብህምና!

አዝናለሁ ሾፌሮች፣ የፍለጋና የነፍስ አድን ሰራተኞች…
የሰመጥኩበትን ባህር ስም ስለማላውቀው፥ አዝናለሁ!

ፈታ በል የስደት ጉዳዮች ክፍል…
ከእንግዲህ ምንም ዓይነት ሸክም አልሆንብህምና!

አመሰግናለሁ ውድ ባህር…
ካለምንም ቪዛና ፓስፖርት ተቀብለኸናልና!

አመሰግናለሁ ዓሳ ሆይ…
ሀይማኖቴንና የፖለቲካ አቋሜ ግድ ሳይሰጥህ ትቀራመተኛለህ!

አመሰግናለሁ የዜና ጣቢያዎች…
እንግዲህ የሞታችንን ዜና ለሁለት ቀናት፣ በየሁለት ሰዓቱ ለ5 ደቂቃዎች ያህል ትዘግቡታላችሁና!

እናመሰግናለን…
ዜናውን ስትሰሙ ስለምታዝኑልን!

አዝናለሁ…
ሰምጫለሁ!

—————————–

P.S. ይህ የሴርያዊ ግጥም፥ ትናንትና በአረብኛ ቋንቋ ብዙ ጊዜ ተነቧል። ግጥሙ መርከብ ውስጥ የነበረ ሰው፥ ከመስጠሙ በፊት የፃፈው ነው የሚሉ ቢኖሩም ማረጋገጥ አልተቻለም። ያም ሆነ ይህ ግን፥ እውነታውን ይናገራልና ሁሉም ያነበው ዘንድ መልካም ነው በሚል ሀሳብ፣ ወደ እንግሊዘኛ ተተርጉሞ በመነበብ ላይ ይገኛል።

አንብቤው፣ ደግሜ አንብቤው… ‘ወደ አማርኛ ብመልሰው እንግሊዘኛውንም አረብኛውንም የማይረዱ ወዳጆች ያነቡታል’ ብዬ በማሰብ ሞከርኩት። ምናልባት ሌላም ሰው ወደሌላ ቋንቋ ቢመልሰው፣ ሌሎች ያነቡትና እንደ ደዚዴራታ ለብዙዎች የሕይወት መመሪያ የሚሆን ነገር ጥሎ ሊያልፍም ይችላል።

ሰላም ይሁንልን!

እንግሊዘኛውን ለማንበብ: ይህን ይጫኑ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s