“በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም”ና፥
የዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም ሬድዮ እንዲዘጋ የብሮድካስቲንግ ባለስልጣን የእግድ ደብዳቤ መፃፉን ተከትሎ፥ ሚሚ “…እንዲዘጋ የሚያዘው ደብዳቤ የህገመንግስታችን አንቀፅ 29 ላይ የተቃጣ የመጋፋት ሙከራ ነው” አለች ተባለ።
➳ ምነው፥ ስንቱ ታታሪ ወጣት የህገመንግስቱ አንቀፅ 29 እየተጣሰበት፣ ሲታሰር፣ ሲሰደድና በፍርሀት ሲርድ፣ ሲሳቀቅ እሷ እንዴት እንዴት ስትል ነበር?
ቀጥላም፥ “ጣቢያው እንዲዘጋ የሚያዘው ደብዳቤ ሲደርሰኝ በጣም ነው የተናደድኩት። በጣቢያው ያሉ ሰራተኞችም ተሸብረው ነበር።” አለች።
➳ ስንቱ በኑሮ ላይ ታችና መሰረት በሌላቸው ክሶች፣ እንዲሁም በባዶ ሜዳ በፍርሀት ሲሸበር እንዴት እንዴት ስታሽቃልጥ ነበር?
ቀጠለች ደግሞ፥ “የሬዲዮ ጣቢያ የሱቅ ደጃፍ አይደለም ማንም ባለስልጣን ተነስቶ ክፈቱ ወይ ዝጉ አይለንም”
➳ ማን ከብት ኖሮ፥ “ውጣ፣ ግባ፣ ታሰር፣ ተፈታ” እየተባለ እንደከብት ሲነዳ ኖረ? እንዲያ በሆነ ጊዜስ እሷ እንዴት ስትል ነበር? አሁንስ ልቧ ምን ይል ይሆን?
“ጥርስ የሌለው አንበሳ” አለች።
➳ ጥርሱን ማንን ሲበላበት አወላልቆት መስሏት? በለው፣ ያዘው፣ ጃስ ስትል አልነበረምን?
.
.
ሌላም ብዙ ብዙ ተባባሉ።
ቅሉ ግን፥ አፋችንን ለመልቀም ካልሆነ በቀር፥
“የዘመድ ልፊያ ልብስ ለመቅደድ ነው”!