እንዳለመታደል…

12767525_991101850982528_2078982365_nአያቶቻችን፥ ደፍሮን የመጣን የጠላት ጦር ስለሰውነት ዋጋ ከፍለው በድል መልሰውት ዛሬም ድረስ አንገታችንን ቀና አድርገን የምንሄድበትን፣ በየትኛውም ቦታ “ኢትዮጵያዊ ነኝ” ስንል፥ ዝም ብሎ ሰው እንዳልሆንን የሚያስመሰክርልንን የድል ታሪክ አበረከቱልን።

ኢትዮጵያን ጠርተን ዓድዋን ያስታወስነው የውጭ አገር ዜጋ፥ በልቡ “ኖር” ብሎ ጎንበስ ቀና ይልልናል። – ይሄ ቁመቱ ነው።

ወገን፥ “ጨርቄን፣ ማቄን፣ ልጄን፣ ቤቴን” ሳይል፥ እስካፍንጫው ከታጠቀ ዘመናዊ ጦር ጋር በጦርና በጎራዴ ገጥሟል። አፍሮም አልገባም፤ በድል እንጂ! – ይሄ ጀግንነቱ ነው።

የአገር ሉአላዊነት እንጂ ብልጭልጭ ስልጣኔ አላጓጓውም። የሰው ልጆች ነጻነት እና ክብር እንጂ፥ ቁሳቁስ አላታለለውም። እኛ እንድንኖር እሱ አለፈ። እኛ እንድንቆም እሱ ወደቀ። – ይሄ ምስጢሩ ነው።

ይኸው እኛ ደግሞ “ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?” በማስባል ዝንታለም የሚያስደንቀውን የአድዋ ድል ታክከን በዘር ተከፋፍለን እርስ በርስ ስለጥላቻ እና ስለዘር፥ ዋጋ ከፍለን እንዋጋለን። ታሪክን ከባለታሪኩ መንጥቀን ለማላቀቅ ላይ ታች እንላለን። ሁኔታችን ሁሉ አዟዙሮ እንደማያይ ነው። ነገራችን ሁሉ ዋጋ እንዳልተከፈለበት ነው። ቆም ብለን የምናደርገውን ብናይ ኖሮም እንኳን በሌላ ሰው፥ በራሳችን ትዝብት ውስጥ መውደቃችንን እንገነዘብ ነበር። እውን፥ የአድዋ ድል የሌላ አገር ድል ቢሆን ኖሮና፣ ታሪኩ ተዘርዝሮልን ብንሰማው ኖሮ፥ አለመደነቅ እንችል ነበር?

አንዳንዴ፥ “ብዙ ያልተደረገልን ሰዎች ብንሆን ኖሮ፣ ብዙ ታሪክና ቅርስ ባይኖረን ኖሮ፣ ተፈጥሮ ለእኛ ባያዳላ ኖሮ፥ ምናልባት ዛሬን ወደ ስልጣኔ ለመሸጋገር እንበረታ ነበር ይሆን?” እላለሁ። ይህም የሞኝ ሀሳብ ነው፤ እንጂ፥ እንዲህ ያለ ድንቅ ታሪክ፥ ዓለም ሲሰማው ሲደነቅበት የኖረን ነገር ማን “የእኔ ባይሆን ኖሮ እበረታ ነበር” ይላል?

የጀግኖቹ በረከት ይደርብን!

#VictoryOfAdwa #Adwa120 #Ethiopia #የአድዋ_ድል

Graphics: Ashu

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s