የደንቢዶሎውን አውሮፕላን ማረፊያ ምርቃት አስመልክቶ በፌስቡክ የተሰጡ አስገራሚ ኮሜንቶች

ምትኩ ዳኜ እንዳጋራን 13516617_308246559519207_8521617860544782900_n

የበረራ አስተናጋጇ “ክቡራን የደምቢዶሎ ተሳፋሪዎች አዉሮፕላኑ በጭቃ ስለተቀረቀረ ወጥተን እንግፋዉ” ስትል አይታያችሁም?

በጭቃ ተይዞ ተሳፋሪው ወርዶ ግፋ ሁላ ሊባል ይችላል ማለት ነው…..ካልሆነ የትራክተር ጎማ ይግጠሙላቸው

Fake port

ጭቃ ማርሽ የሌለው አውሮፕላን ደምቢ ዶሎ መብረር የለበትም።

73 ሚልየን ብር ለደን ምንጠራ ነው? ሃሃሃ

በቃ ተገንብቷል አልኳችሁ ተገንብቷል፡፡ ሜዳው ራሱ ተገንብቻለሁ ብሎ እያመነ እናንተ ምነዉ?

አሞራ ራሱ እሺ ብሎ ሚያርፍ አይመስለኝም ክክክ

ዝናብ ሲዘንብ አውሮፕላኑ ቦቲ ጫማ አድርጎ እንደሚያርፍ ተስፋ እናደርጋለን

ቀልድ ነው አደል? በማርያም እኔ እልገባኝም ንገሩኝ

ማ ነበረ ከጥይትና ከርሀብ የተረፈውን ህዝብ በሳቅ እየገደሉት ነው ያለው?

EBC ደግሞ ገንዘቡን ወደ 33 ሚልዮን አውርዶታል። አብሽር ውለን ካደርን ገንዘቡ ወደ 73 ሺህ ብር መውረዱ አይቀርም። ዋናው ትዕግስት ነው!

ኪኪኪኪኪ….. ከመሀከላቸው አንድም ሰው የሚያገናዝብ ይጥፋ እንዴ? እረ እነዚህ ሰዎች ወደ ፃድቃኔ ማርያም ሄደው ሁለት ሰባት ከፍልጥ ጋር ሳያስፈልጋቸው አይቀርም፨

የእብድ ቀን አይመሽ አለች እማማ. . . ሳሩን ለማሳጨድ ነው 73 ሚሊዩን የተከፈለው?

hahahahah የእርሻ አውሮፕላን ነው?እያረሰ ነው እሚመስለው’ኮ

ዋውውው በቆሎ ቢዘራበት ምን ይመስላችኋል?

73ሚሊ.. አንድ አውሮፕላን ቢገዙበት አሪፍ ነበር ከጎደለ እንሞላላቸዋለን እንኩአን ይችን የስዊዝን ካዝና ሞልተነው የለ?

ኧረ ክረምት ነው ፕሌኑ እንዳይሰምጥና ሳይደላኝ እንዳልስቅ እባካችሁ

ኣውሮፕላኑ ችግር ገጥሞት የሆነ እርሻ ውስጥ ያረፈ ነው ሚመሰለው!

እረ ጎበዝ ይች አገር ወደ ሄት እየሄደች ነው???????? ያሳዝናል እንዴት የአንድ አገር መንግስት ሁሉ ደነዝ ሁሉ ድንጋይ ምነው ይሄ እኮ 21 ሴንቸሪ ነው ምነ እንደበግ ማሰቡን ብተውት!!!!!!

የተሰራው የፈረስ ጉግስ መጫዎቻ ነው። አይዞኝ እናት ሀገሬ

አውሮፕላን ጭቃ ላይም ያርፋል እንዴ!!!ወይ አለማወቅ፡፡

ምንድነው ነገሩ? ክረምት ክረምት የት ሊያርፍ ነው?

ከወያኔ ‘ብልጣ ብልጥ’ ስልቶች አንዱ እነሱ ፈትፍተው እየበሉ ሌላውን አፉን ወጥ መቀባት ነው። የአክሱምና የደምቢዶሎው የጢያራ ማረፍያዎች የዚህ ማሳያ ናቸው።

ለማስመረቅ እንኳን በኮብል ስቶን ሸፈን ቢያረጉት

ከአሁን በኃላ ወደኪስ ነው ወንድሜ እየተበደሩ swize ባንክ እንደ ባስኬት ቦል ፕሮጀክት እንዳትጠብቅ

የሌቦች ነገር ዛሚን ደግሞ ብትሰማ 112 ሚሊዮን ሳትል አትቀርም።

እነዚህ ሰዎች ሀገሪቷን በዕውቀት ሳይሆን በድግምት ነው የሚመሩት

ሰበር ዜና . በደምቢዶሎ። ከ33 ;42; 73 ሚሊዮን ብር በላይ የጨረሰው የጭቃ አየር ማረፊያ ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ ።

ግብርና መር—— አውሮፕላን ማረፊያችን

የሚሰማቸው ካገኙ ይህ አውሮፕላን ማረፊያ ከአፍሪካ 1ኛ ከአለም 2ኛ መሆኑ ይነገረናል ከአፍሪካ1ኛ ስል ምን ትዝ አለኝ ኢትዬዾያዊው ሰላይ ጀምስ ቦንድ ሞላ ግን እንዴት ነው ??!!!!!!

አስፓልቱ እኮ ከስር ነው እንዳይጎዳ ነው ከላይ ጭቃ የቀቡት እንዳይበላሽ!!! እርርርርርርርር….

እኔ እኮ በቴክኒክ ምክንያት የአንድ ገበሬ እርሻ መሬት ላይ ፓይለቶቹ ያሳረፍት መስሎኝ ነበር ።

የደምቢ ዶሎ ኤርፖርት ለትግራይ ህዝብ ምኑ ነው? ሟቹ ጠሚ በኮፒራይት እላይ ስሄድ እንዳይከሰኝ

ይሄን ሚሊዩን የሰው ስም አደረጉት እኯ ወይ ነዶ

አውሮፕላን በአፈር ላይ ማብረር ተጀመረ እንዴ እኛኮ ሁሌ አንደኛ ነኝ ታድለን

ታዲያ ለምንድነው ህዝብ ቢጠላቸው የሚደንቃቸው?

ወይ ጉድ…

ከዓመት ከምናምን በፊት…
 
“አብሬያቸው ብሰራ” ከምላቸው፣ ጥሩ ስሜት ካሉኝ መሥሪያ ቤቶች መካከል በአንዱ የሥራ ማስታወቂያ መውጣቱን ጋዜጣ ላይ ተመልክቼ ለማመልከት አሰብኩና የትምህርት እና የሥራ ማስረጃዎቼን አደራጅቼ ሄድኩ። (መቼም አብዛኛው ቅጥር በፖለቲካ አቋም፣ በትውውቅና በዝምድና እንደሆነ ባላጣውም፥ በምናልባት ነበር ሙከራው።)
 
ከወጡት ሶስት የሥራ መደቦች እኔ ለማመልከት የፈለግኩት “managing director” ይል የነበረውን የሥራ መደብ ነበር። (ቀሪዎቹ ሁለቱ Data Encoder እና Secretary ነበሩ።) መስፈርቱን በበቂ ሁኔታ ስለማሟላ “ለቃለ መጠይቅ ፈተና ቢጠሩኝ እንኳን…” የሚል ጉጉት ነበረኝ።
 
ቢሮው ደረስኩኝና የሰው ሀብት አስተዳደሯን (መሰለችኝ) “ጤና ይስጥልኝ፣ የሥራ ማስታወቂያ አይቼ ለማመልከት ነበር።” አልኳት።
 
“Data encoder ነው?” አለችኝ። (ሶስተኛው መደብ ‘secretary’ ስለነበረ ሴቶችን ብቻ መጠበቋም አብሽቆኝ ነበር።)
 
“አይ ለማኔጂንግ ዳይሬክተር መደብ ነው።” አልኳት።
 
ገለማመጠችኝ አይገልጸውም።
 
“ማስታወቂያውን በደንብ አይተኸዋል? መስፈርቱ ብዙ ነው።” አለችኝ።
 
“አዎ! ስለማሟላ ነው የመጣሁት። ዶክመንቶቼን ይዣቸዋለሁ።” አልኳት።
 
“ማስተርስ ዲግሪ ነው የሚጠይቀው።” አለች።
 
“Sure, አለኝ” አልኩ።
 
“በአስተዳደር መደብ የሰራም ይላል…” አለች
 
“አዎ ሰርቻለሁ። እንደውም አሁን የምሰራውም በአስተዳደር መደብ ነው።”
 
አልተዋጠላትም። ዶክመንቶቼን እየተቀበለችኝ፣ “ብዙ ሰው አመልክቷል። ባትደክም ግን ጥሩ ነበር” ብላ አጉተመተመች። ማኅተሞቹን አፍጥጣ መመርመር ያዘች።
 
“ቆይ ግን ምን ዓይነት ሰው ጠብቀሽ ነበር?… ለማኔጂንግ ዳይሬክተርነት የሚያመለክተው ሰው እንዴት መሆን አለበት ብለሽ ነው?” አልኳት።
 
መልስም አልሰጠችኝም።
 
ተናድጄ ቀጠልኩ። “ሁኔታሽ ደስ አይልም። ብቀጠር እኮ ምናልባት አለቃሽ ነው የምሆነው።” አልኩ።
 
እርሷ እቴ ምንም አልመሰላት። (በልቧ “ኡኡቴ” ሳትልም አይቀር)
 
‘ስወጣ የቅርጫት ሲሳይ ታደርገዋለች።’ ብዬ ባስብም የተቀበለቻቸውን ዶክመንቶች ዝርዝር መመዝገቢያዋ ላይ መዘገበችኝ እና ፈረምኩ።
 
“ሳስበው ስራውን ብዙም አልፈልገውም። ለፈተና መጠራቴን ግን እፈልገዋለሁና ዶክመንቴ ቅጥር ኮሚቴው እጅ መድረስ አለመድረሱን እከታተላለሁ። ደህና ይዋሉ።” ብያት ሄድኩኝ።
 
* * *
 
ከወራት በፊት ደግሞ…
 
ለአንድ የአደራ መልእክት… የቤትና የቢሮ እቃዎች ሱቅ ሳይ፥ ተልኬ የነበረውን መግዛት የነበረብኝ እቃ ትዝ ብሎኝ ገባሁና ዞር ዞር ብዬ አይቼ፥
 
“ይሄ ስንት ነው?” አልኳት።
 
“ለቤት ነው የሚሆነው” አለችኝ።
 
በልቤ “ሆ” ብዬ… “አዎ እኔም ለቤት ነው የፈለግኩት።”
 
“ማለቴ ለመኖሪያ…”
 
“አዎ እኮ ለመኖሪያ። ቤት ያለውና የሌለው በድምጽ ይለያል እንዴ?” እንደጨዋታ ነበር ያሰብኩትና ያልኩት።
 
የተጋነነ ብር ነግራኝ… አያይዛ፥ “ግን ከዚህ ወረድ ብሎ አንድ ቤት አለ። ጠይቀሃል እዛ። ይረክስልሃል።” ብላኝ እርፍ።
 
* * *
 
በዚህ ሰሞን…
 
የሰው አገር ጠብ እርግፍ ሲታይ ደግሞ፥ የሚገዛውን እና የማይገዛውን፣ የሚመጥነውን እና የማይመጥነውን ሰው በዐይን አይተው የሚለዩት የአገሬ ልጆች በዐይኔ ዞሩ። የአገር እና የአገር ልጅ ነገር እንደው ባሰቡት ቁጥር ግርም ይላል፤ …ይኼ ይኼም እንደ ደህና ቁምነገር ይናፍቃል!
 
አልኩኝም… ወይ ጉድ!!!