“ስለ ትናንሽ አለላዎች” የዮናስ አ. መጽሐፍ

ወጣትነት እንደቢራቢሮ ተራራ የተከመረ ቀለም ነው። ብዙ መልክ ያለው ግን በቀላል ንፋስ እንደአመዳይ የሚበተን። ምናልባት ማሰብ ከሚገባን በላይ እናስባለን። ወይም በተቃራኒው።

*

ጠይም ባቶች የፈጠረ ማነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ቆንጆ አድርጎ የሚፈጥር ማነው? ጦሳ አይደለም ወይ? የሚያነሳ ማነው? የሚጥልስ? የሚያድን ማነው? የሚገድልስ? …

ሞት ሲመጣ እንዴት ነው? እንደነፋስ? እንደ ደመና፣ እንደ ጭጋግ መሰስ ብሎ? እንደ እንግዳ ድንገት ከተፍ? እንደሽታ፣ እንደሰንደል ጢስ? እንደምሽት፣እንደ ጨለማ?

*

አንድ ቀን ግን በቀትር ብቻቸውን ተቀምጠው ሲያንጎላጁ ሳለ፥ መጣ። ተጠርቶ የሚመጣ ሞት የለም። ዐይኖቻቸውን ሲከፍቱ ነጭ ሸማውን አጣፍቶ ለብሶ ፊት ለፊታቸው ተገትሯል። ከቤታቸው ውስጥ የሰንደል ጢስ ጉበኑን እየላሰ ወደ ውጭ ይተናል።
“ውይ ሞትዬ፥ መጣህልኝ?”

“መጣኹኝ።” እየፈገገ፣ እየተሽኮረመመ፣ ደግሞ እየተንጎማለለ።

“በል ልብሴን ልልበስ፣ ልተጣጠብ ጠብቀኝ።” አሉት።

እየሣቀ ቀረባቸው…

*

“…ምናልባትም ፀሓያማ የመስከረም ከሰዓቶቻችንና በጠራ የታህሳስ ሰማይ በምሽት ያየናቸው ወርቃማ አብረቅራቂ ከዋክብት በትናንሽ ሓልዮቶቻችን ውስጥ የተከሰቱ ትላልቅ ተዓምራቶች ሊሆኑ ይችላሉ። አማልክት ነንና።
ምናልባት ሕይወታችንን ሙሉ የምንባክነው ያሳለፍነውን መልካም ነገር ፍለጋ ይሆናል። መዋቲ ነንና። ደግሞም ስግብግቦች። ህይወት ክብ ናት የሚሉ አሉ።
ምናልባት ይሄ ኹሉ ነገር፣ የኾነውና ያልኾነው፣ ገና የሚኾነውም ኹሉ በሙሉ አእምሯችን ውስጥ የተጋነነ የቀን ሕልም ነው።
ወይም ደግሞ ምናልባት ኹሉም እንደምናየው እንደምንሰማው መጠን እውነት ነው።
ምናልባት . . .”

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s