ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በዜማ፣ በግጥም እና በቅንብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገው ውዱ ኤልያስ መልካ የሰላም እረፍት ይኾንለት ዘንድ እንመኛለን። ፈጣሪ ነፍሱን በቀኙ ያሳርፋት። ለቤተሰብ፣ ለሙያ አጋሮቹ እና ወዳጆቹ መጽናናትን እንመኛለን። እጅግ በላቁ ስራዎቹ ዘወትር እንደተወደደ እና፣ በክብር በልባችን እንደተዘከረ ይኖራል። ስለዚህም፥ አረፈ እንጂ ሞተ አንልም።
Month: October 2019
“ጎዳናው እስኪቋጭ” የአሳዬ ደርቤ አዲስ መጽሐፍ
ሽግግሩ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በየቀኑ የሚሰሙ ቅስም ሰባሪ ሰበር-ዜናዎች ከመብዛታቸው የተነሳ ለማስታወስ ያዳግታል፡፡ እመርታዎቹ ደግሞ የማይታዩና የማይጨበጡ በመሆናቸው ማይክሮስኮፕ ላይ ተጥዶ ምርምርና ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ከለውጡ ወዲህ የተቀጠፉት ነፍሶች ይሄን ለውጥ ለማምጣት ከተሰውት እየበለጠ ነው፡፡ ይሄም ሆኖ ግን ሰውዬው በምታለቅስ አገር ላይ ፈገግ እንዳለ ቀርቷል፡፡ ሁሉም ነገር የሚሆነው በእሱ ይሁንታ ይመስል፣ በተደናገረው ሕዝብ መሀከል በሁለት ዙር ግንብ ካሳጠረው ቤተ-መንግሥቱ ውስጥ ሆኖ በቃላት ይፈላሰፋል፡፡
*
የመጻፍ ሙዳችን እየመጣ ነው፡፡
ስለምን እንጻፍ? ስለምን እንፈላሰፍ?
“ሽግግር- ከችግር ወደ ችግር” የሚል ርዕስ አስምረን ችግሮቻችንን እንዘርዝር?
ነው ወይስ…
“ለውጥ- ከማጥ ወደ ማጥ” የሚል አጀንዳ ይዘን “እንደ አገር” አብረን እንስመጥ?
ድል- ከትግል ወደ ትግል
ድልድይ- ከገደል ወደ ገደል
ምናምን፣ ምናምን እንበል?
ወይስ?
ለውጡ እንዳይቀለበስ
ትችታችን ጋብ አርገን- ንፋሱን ጋልበን እንንፈስ?
*
እኛን ያላዩ ፈረንጆች-በእውቀት፣ በሀብቱ የታደሉ
“A problem well-stated is a problem half solved” ይላሉ፤
“ሙሉ በሙሉ የታወቀ ችግር በከፊል ምላሽ አግኝቷል” እንደ ማለት፤
ታዲያ የኛ ደዌ እና ተውሳክ- ሙሉ በሙሉ ታውቆ ሳል- እንዴት መፍትሄ ታጣለት?
ለዶክተሩ የነገርነው በሽታችን ሊድን ቀርቶ ስለምን ነው የባሰባት?
መልሱ ቀላል ነው!
በሽታችን ገሃድ ወጥቶ-እንደ ብቅል- ከጸሐይ ላይ ቢነጠፍም
መርፌና ሐኪም ከለገመ- እንኳን ታፋ- ቅቤ አይወጋም፡፡
በሺህ ቃላት ቢቀባቡት- የመርዝ ውህድ- ሽሮፕ ሆኖ አይፈውስም፡፡
በመሆኑም…
ዶክተር በምድሩ ሳለ- ቅስቻችንን ያበረታው- የተያዝነው በጣር፣ ሲቃ
“ሕመማችን ታውቆ ሳለ- መዳኒቱን ተነፍገን ነው” ብዬ ላብቃ፡፡