Category: ጠይም መጽሐፍት
መባቻ (በያሬድ ጌታቸው)
ቢገባን
ዛሬን ስንቀመጥ ፣ ከምቾቱ ወንበር
ትናንትን ባንረሳ ፣ ነገ እንዴት ውብ ነበር!
መንደርደሪያ
ራስን መሆን ከራስ፣ ራስን መሆን ከሌሎች የተውጣጣ ገዢ ሀሳብ አመለካከት አስተሳሰብ እምነት ሊቀዳ ይችላል ። ማንም በራሱ ብቻ ችሎ አይቆምም ወይ በሰው አሊያም በተፈጥሮ ይደገፋል ። ማንም ፍልስፍናውን ከሌለ ነገር ላይ ተመስርቶ አይፈላሰፍም ወይም አያሰላስልም የሌለ ሃሰብ የለም የሌለ ምንለው ካለው ይነሳል ። የኔ የምትለው ሃሰብ ከብዙ በጎነት ወይም ከብዙ ክፋት እየተቀዳ በሕይወት ምልልስ ላይ ደጋግመህ የተለማመድከው ፣ የኖርከው የኖርክለት አስተሳሰባዊ የአንተነት ማንነት ነው ። ራስን ካልቃኙበት መሆንን ያልሆነ መምሰል ልክነት አይደለም ። አይደለም መምሰል ራስን መሆንም ልክነቱ ለራስና ሌሎች በልክነት ለሚመለከቱት ብቻ ነው ። እናም እኔም ራሴን የሆንኩበትን መሻቶቼን የቃተትኩበት ፣ ያሰላሰልኩትን፣ ስሜቴ በሁሉም አውድ የተነካሁበትንና ምናቤ በነጎደበተን መንገድ ተከትዬ ለእኔ መጀመሪያ ለእናንተ ደግሞ ስጦታ በሆነችው “መባቻ” የበኩር ስራዬ ራስን በመሆን ውስጥ ራስን መግለጥ ባተ ፡፡
“ዐይኔ ዓለም አየ”፤ የላሊበላ ልጅነት እና የቦታ ፍልስፍና (አጭር ቆይታ ከዶ/ር ይርጋ ገላው ጋር) | Ethio Teyim | Episode 14
ተማሪዎቹ የት ገቡ? አስተያየት የመስጠት ባህላችን እና እኛ! “ምናለ” (የመስፍን አሸብር ግጥም በስንዱ አበበ) | Ethio Teyim | Episode 13
የሥራ እና የሕይወት ሚዛን፥ ጤናችንን ስለመጠበቅ፤ የአይዳ ታደሰ ግጥም፣ እና የሚያሸልም ጥያቄ | Ethio Teyim | Episode 11
ከመጽሐፍቱ መቃጠል ባሻገር… ከ”ጳጳሱ ቅሌት” እስከ “ጳጳሱ ስኬት” ቢታሰብስ | Episode 4
“ጎዳናው እስኪቋጭ” የአሳዬ ደርቤ አዲስ መጽሐፍ
ሽግግሩ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በየቀኑ የሚሰሙ ቅስም ሰባሪ ሰበር-ዜናዎች ከመብዛታቸው የተነሳ ለማስታወስ ያዳግታል፡፡ እመርታዎቹ ደግሞ የማይታዩና የማይጨበጡ በመሆናቸው ማይክሮስኮፕ ላይ ተጥዶ ምርምርና ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ከለውጡ ወዲህ የተቀጠፉት ነፍሶች ይሄን ለውጥ ለማምጣት ከተሰውት እየበለጠ ነው፡፡ ይሄም ሆኖ ግን ሰውዬው በምታለቅስ አገር ላይ ፈገግ እንዳለ ቀርቷል፡፡ ሁሉም ነገር የሚሆነው በእሱ ይሁንታ ይመስል፣ በተደናገረው ሕዝብ መሀከል በሁለት ዙር ግንብ ካሳጠረው ቤተ-መንግሥቱ ውስጥ ሆኖ በቃላት ይፈላሰፋል፡፡
*
የመጻፍ ሙዳችን እየመጣ ነው፡፡
ስለምን እንጻፍ? ስለምን እንፈላሰፍ?
“ሽግግር- ከችግር ወደ ችግር” የሚል ርዕስ አስምረን ችግሮቻችንን እንዘርዝር?
ነው ወይስ…
“ለውጥ- ከማጥ ወደ ማጥ” የሚል አጀንዳ ይዘን “እንደ አገር” አብረን እንስመጥ?
ድል- ከትግል ወደ ትግል
ድልድይ- ከገደል ወደ ገደል
ምናምን፣ ምናምን እንበል?
ወይስ?
ለውጡ እንዳይቀለበስ
ትችታችን ጋብ አርገን- ንፋሱን ጋልበን እንንፈስ?
*
እኛን ያላዩ ፈረንጆች-በእውቀት፣ በሀብቱ የታደሉ
“A problem well-stated is a problem half solved” ይላሉ፤
“ሙሉ በሙሉ የታወቀ ችግር በከፊል ምላሽ አግኝቷል” እንደ ማለት፤
ታዲያ የኛ ደዌ እና ተውሳክ- ሙሉ በሙሉ ታውቆ ሳል- እንዴት መፍትሄ ታጣለት?
ለዶክተሩ የነገርነው በሽታችን ሊድን ቀርቶ ስለምን ነው የባሰባት?
መልሱ ቀላል ነው!
በሽታችን ገሃድ ወጥቶ-እንደ ብቅል- ከጸሐይ ላይ ቢነጠፍም
መርፌና ሐኪም ከለገመ- እንኳን ታፋ- ቅቤ አይወጋም፡፡
በሺህ ቃላት ቢቀባቡት- የመርዝ ውህድ- ሽሮፕ ሆኖ አይፈውስም፡፡
በመሆኑም…
ዶክተር በምድሩ ሳለ- ቅስቻችንን ያበረታው- የተያዝነው በጣር፣ ሲቃ
“ሕመማችን ታውቆ ሳለ- መዳኒቱን ተነፍገን ነው” ብዬ ላብቃ፡፡
“ስለ ትናንሽ አለላዎች” የዮናስ አ. መጽሐፍ
ወጣትነት እንደቢራቢሮ ተራራ የተከመረ ቀለም ነው። ብዙ መልክ ያለው ግን በቀላል ንፋስ እንደአመዳይ የሚበተን። ምናልባት ማሰብ ከሚገባን በላይ እናስባለን። ወይም በተቃራኒው።
*
ጠይም ባቶች የፈጠረ ማነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ቆንጆ አድርጎ የሚፈጥር ማነው? ጦሳ አይደለም ወይ? የሚያነሳ ማነው? የሚጥልስ? የሚያድን ማነው? የሚገድልስ? …
ሞት ሲመጣ እንዴት ነው? እንደነፋስ? እንደ ደመና፣ እንደ ጭጋግ መሰስ ብሎ? እንደ እንግዳ ድንገት ከተፍ? እንደሽታ፣ እንደሰንደል ጢስ? እንደምሽት፣እንደ ጨለማ?
*
አንድ ቀን ግን በቀትር ብቻቸውን ተቀምጠው ሲያንጎላጁ ሳለ፥ መጣ። ተጠርቶ የሚመጣ ሞት የለም። ዐይኖቻቸውን ሲከፍቱ ነጭ ሸማውን አጣፍቶ ለብሶ ፊት ለፊታቸው ተገትሯል። ከቤታቸው ውስጥ የሰንደል ጢስ ጉበኑን እየላሰ ወደ ውጭ ይተናል።
“ውይ ሞትዬ፥ መጣህልኝ?”
“መጣኹኝ።” እየፈገገ፣ እየተሽኮረመመ፣ ደግሞ እየተንጎማለለ።
“በል ልብሴን ልልበስ፣ ልተጣጠብ ጠብቀኝ።” አሉት።
እየሣቀ ቀረባቸው…
*
“…ምናልባትም ፀሓያማ የመስከረም ከሰዓቶቻችንና በጠራ የታህሳስ ሰማይ በምሽት ያየናቸው ወርቃማ አብረቅራቂ ከዋክብት በትናንሽ ሓልዮቶቻችን ውስጥ የተከሰቱ ትላልቅ ተዓምራቶች ሊሆኑ ይችላሉ። አማልክት ነንና።
ምናልባት ሕይወታችንን ሙሉ የምንባክነው ያሳለፍነውን መልካም ነገር ፍለጋ ይሆናል። መዋቲ ነንና። ደግሞም ስግብግቦች። ህይወት ክብ ናት የሚሉ አሉ።
ምናልባት ይሄ ኹሉ ነገር፣ የኾነውና ያልኾነው፣ ገና የሚኾነውም ኹሉ በሙሉ አእምሯችን ውስጥ የተጋነነ የቀን ሕልም ነው።
ወይም ደግሞ ምናልባት ኹሉም እንደምናየው እንደምንሰማው መጠን እውነት ነው።
ምናልባት . . .”