Advertisements

Recent Posts - page 2

 • “ሴቶች አስቂኝ ናቸው”

  ከ2 ሩም ሜቶቼ ጋር፥ ፒንች ውስኪ በ3 ብርጭቆ ቀድተን አጋጭተን ተጎነጨን። ከጥቂት ቆይታ በኋላ አንደኛው ‘ኖርዝ ካሮላይና የሚሄድ ልጄን አውሮፕላን ማረፊያ አደርሳለሁና ልሂድ’ ብሎ ተሰናብቶን ወጣ። ሬሜ ይባላል። ስለእሱ ሌላ ቀን እንጫወታለን።   ከዴቪድ ጋር ለጥቂት አፍታ ዝም ተባብለን ስለሚስቱ… Read More ›

  Advertisements
 • ከአዲሱ ክፍል ተጋሪዬ ጋር

  በሬ ተንኳኳ።   የከፈትኩትን ሙዚቃ አስቁሜ፣ “ማነው?” እያልኩ ተነሳሁ፣ ከሩምሜቶቼ (ክፍል ተጋሪዎቼ) ውጭ ሌላ ማንም እንደማይሆን ልቤ እያወቀው።   አዲሱ ክፍል ተጋሪዬ ዴቪድ ነው። ጠርሙስ እና ሲኒ ይዞ፣ ፈገግታ ተሞልቶ “ሰላም” አለኝ።   “ሰላም ዴቪድ። እንዴት ዋልክ?” አልኩት   በቀኝ… Read More ›

 • ከአዋላጅ ነርስ ወዳጄ ጋር ገጠመኝ

  ጊዜ ሳገኝ ስለህክምና ባለሞያዎች የማስታውሰውን እጽፋለሁ ባልኩት መሰረት፥   ጎሮ የሚባል ጤና ጣቢያ ስር ያሉ የጤና ኬላዎች (health posts) የCHIS (community health information system) የሥራ ላይ ስልጠና ለመስጠት ከአንዲት አዋላጅ ነርስ የስራ ባልደረባዬ ጋር እንሄድ ነበር።   ነገሩ፥ የትራንስፖርት ችግርም… Read More ›

 • ለአገሬ የህክምና ባለሞያዎች

  በአስተዳደር በደል ምክንያት እጀ ሰባራ ለምትደረጉ፣   በsterilization መሳሪያ እጥረት ወይም በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ጉልቻ ጥዳችሁ መሳሪያ ትቀቅሉ ዘንድ ለተፈረደባችሁ   ደም ለግሳችሁ ነፍስ ለማትረፍ ለምትተጉ   በላቦራቶሪ እና በዘመናዊ ዶክመንቴሽን ችግር ምክንያት የምርመራ ውጤት ለሚዘበራረቅባችሁ   የሀሰት ሪፖርት እንድትልኩ… Read More ›

 • ካለ ሰው…

  ከነድህነቱ ወዘናው ፊቱ ላይ ጨፍ ያለ ምስኪን፤ ዘሩ ምን ሆነ ምን፥ ፈገግታው ከልቡ ፈልቆ ፊቱ ላይ፣ ጥርሱ ላይ፣ ዐይኑ ላይ፣ ግንባሩ ላይ ሁሉ የሚከለበስ ድሃ። ቂጡ ሁላ የሚስቅለት ዕድለኛ፥ ምንም የሌለው፣ ሁሉም ያለው። የአዲስ አባ ሰው፣ የአገር ሰው!   ገመድ… Read More ›

 • ያልተዘመረላቸው የኑሮ ወታደሮች

  የተረሱ፣ የተዘነጉ ወታደሮች…. ያልተዘመረላቸው የሕይወት ጀግኖች፣ ከኑሮ ጋ ትንቅንቅ ገጥመው በየበረሀው የቀሩ፣ እና በየአረብ አገራቱ የሚንከራተቱ እህት ወንድሞች አሉ።   የእናታቸውን ነጠላ ለመቀየር የተለሙ፣ የመሶቧን ልምላሜ ለማስጠበቅ የተመሙ፣ የቤታቸውን ዳር ድንበር ለማስከበር ልጅነታቸውን የገበሩ ብዙ ወጥቶ አደር ወገኖች አሉ። የቤተሰባቸውን… Read More ›

 • የጉዞ ነገር…

  ሁሉም የአፍሪካ አገራት ነዋሪዎች ወደኢትዮጵያ ለመግባት፣ በደረሱ ጊዜ ቪዛ ማግኘት የሚችሉበት አሠራር፣ ከኖቬምበር 10 ይጀምራል ተብሎ ነበር። (እንዴት ሆነ እንኳን “እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲሁም ጤዛ ነሽ” ይላሉ። የደህንነት ሁኔታው እንዲህ በሆነበት ጊዜ ጣጣው ብዙ ነው።   እሱን ባሉ በ20 ስንተኛ ቀኑ፥… Read More ›

 • ሴት ነሽና

  ሴት ነሽና፥ ሰውነቱን፣ ክብሩን ትቶ፣ ቀሚስሽን ወንድ ይለካል ደግሞ ሲለው ተንጠራርቶ ተጠራርቶ… ደፍሮ ይነካል፤   ሴት ነሽና፥ “ተው” ብትዪው፥ እንደመብቱ “ዝም በይ” ይላል በአንደበቱ፤ ማንም የለም “ተው” የሚለው፣ ሁሉም አጋዥ አበርቺው ነው፤   ሴት ነሽና፥ የሀሳብሽን ቁመት ልቀት የህልምሽን ስፋት… Read More ›

 • ስለሀሳብ ልዕልና ሲወራ…

  ምርጫውን ፍትሀዊ እና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ የተደረገው የቃል ተስፋ መልካም ነው። እግዚግዚአብሔር ፈቅዶ ምርጫው ነጻ ሆኖ ቢከናወን ግን፣ ኢህአዴግ በምን ቁመናው ሊቀጥል ይችላል? 🤔   በርግጥ “ከማያውቁት መልዐክ የሚያውቁት ሰይጣን” በሚል ብሂል የሚገብርላቸው ሊኖር ቢችልም ቅሉ፥ ለክፋታቸው ሲነዙት የኖሩት የብሄር አጀንዳ… Read More ›